RedBlueDark SmallMediumLarge NarrowWideFluid
ALL NEWS
Addis Ababa constructing houses with 5.7 billion birr PDF Print E-mail
Written by eskinder   
Saturday, 09 February 2013 15:12

Addis Ababa City Administration is managing the construction of houses with 5.7 billion birr. This is according to Construction and Housing Development Bureau of the City.

 

 

In the last two quarters, 3 billion of the finance has been spent to keep the construction rolling.


 

According to the report, the performance of the quarters was improved relatively as it is well organized. The hope is this year will see the completion of 20,000 houses in the city.

 

Read more...
 
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመከላከያ ሰራዊት ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀው ኤግዚብሽን ተከፈተ PDF Print E-mail
Written by eskinder   
Saturday, 09 February 2013 15:10

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመከላከያ ሰራዊት ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ዓርብ የካቲት 1/2005 በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተከፈተ፡፡

 

 

ከየካቲት 1 እስከ 7/2005 የሚቆየው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመከላከያ ሰራዊት ቀን ክብረ በዓል ″ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችን እንደተጠበቀ ይኖራል″ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለው፡፡


የክብረ በዓሉ አንድ አካል የሆነው አውደ ርዕይም በኤግዚብሽን ማዕከልና በመስቀል አደባባይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም አማካኝነት ለጉብኝት ክፍት ሆኗል፡፡


በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ካሳ ተክለብርሃንና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳና ከጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ እንዲሁም ከሌሎች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር እንግዶች ጋር አውደ ርዕዩን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ፡፡

 

Read more...
 
የኢፌዲሪ አየር ኃይል የፈፀማቸው አንፀባራቂ ገድሎች የሠራዊቱ ሁለንተናዊ ብቃት ማሳያ መሆናቸው ተገለፀ PDF Print E-mail
Written by eskinder   
Saturday, 09 February 2013 15:08

የኢፌዲሪ አየር ኃይል በየተሰማራበት የግዳጅ ውሎዎች ያሳየው ጀግንነትና የፈፀማቸው አንፀባራቂ ገድሎች የሠራዊቱ ሁለንተናዊ ብቃት ተጨባጭ ማሳያ መሆናቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና የሪፎርም ክላስተር አስተባባሪ እና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስር አቶ ሙክታር ከድር ገለፁ፡፡

 

 

Read more...
 
ከዛሬ ጀምሮ ለ7 ቀናት የሚቆየው የመከላከያ ሳምንት በሃገራችን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው PDF Print E-mail
Written by eskinder   
Saturday, 09 February 2013 15:05

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2005 ፣ ከዛሬ ጀምሮ ለ7 ቀናት የሚቆየው የመከላከያ ሳምንት በሃገራችን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

''ህገ-መንንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዛባዊ ባህሪያችን እንደተጠበቀ ይኖራል'' በሚል መሪ ቃል  ነው ፥ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከበረ ያለው።

የበአሉ ዋና መርሃ ግብር የሆነው የሃገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚያሳይ አውደ ርዕይ ፥ በኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ተከፍቷል።

አውደ ርዕዩን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣ ዲፕሎማቶች ፣ የተለያዩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየጎበኙት ነው።

የኢፊዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ እንዳሉት ፥ የመከላከያ ሰራዊት ሃገሪቱ የጀመረችው እድገት እንዳይቋረጥ ዘብ ከመቆም ባለፈ በተለያዩ ልማቶች ላይ ከፊት በመቅደም ለኢትዮጵያውያን ምሳሌ መሆን ችሏል።

Read more...
 
የመንግስት ተሽከርካሪዎችን ለግል ጥቅም የማዋል ድርጊት እየተበራከተ ነው PDF Print E-mail
Written by eskinder   
Saturday, 09 February 2013 15:05

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2005 ፣  አንዳንድ የስራ ሃላፊዎችና ሹፌሮች የመንግስት ተሽከርካሪዎችን ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በስራ ቀናት ለግል ጥቅምና ለአልባሌ ተግባራት ስራ በማይሰራበት በመዝናኛ ስፍራዎችና በሌሎች አልባሌ ቦታዎች ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላል።

ሃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡና ለህዝብ ጥቅም ብቻ የመንግስትን ተሽከርካሪዎችን የሚጠቀሙ ሃላፊዎችና አሽከርካሪዎች  እንዳሉ ሁሉ  ለግል ጥቅምና  አጸያፊ ተግባራት መፈፀሚያነት የሚጠቀሙም  እንዳሉ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘጋቢ ተዘዋውሮ በተመለከታቸው ቦታዎች ለመታዘብ ችሏል።

በአዲስ አበባ ፒያሳ፣ ካዛንቺስ፣ 22 ፣ በተለይ ቺቺኒያ ፣ ቦሌ እንዲሁም ፥ በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙት ሱሉልታ፣ ዱከም፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማና በሌሎችም አካባቢዎች ይህ ተግባር የሚፈፀምባቸው አከባበቢዎች ናቸው ።

እየተገነቡ ባሉ ረጃጅም ህንጻዎችና በየመጠጥ ቤቶች ጥጋ ጥግ ተኮልኩለው ስራ በሌለበት ከተማዋን የሚያካልሉ ፥ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጪ ረዥም ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው በስመ መዝናናት ነዳጅ የሚያባክኑም እንዳሉ ጣቢያችን ደርሶበታል።

እነዚህ ተሽከርካሪዎች ኮድ 4 እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሆኑ ኮድ 3 እና አንዳንዴም የመንግስት ሆነው ታርጋቸው በግል ተሽከርካሪዎች የተቀየሩ ተሽከርከኛሪዎች  እስከ ከባድ ወንጀል እንደሚፈፀምባቸው ተስተውሏል ።

ለመንግስትና ለህዝብ ስራ የተሰጣቸውን ተሽከርካሪዎች ለጭነት አገልግሎት ፣ ለኮንትራት ስራ ፣ ለልጆቻቸው ማለማመጃና ለሌሎችም ተግባራት እንደሚያውሉት ነው ጥቆማቸውን ለጣቢያችን የሰጡ  ግለሰቦች  የገለፁልን።

 

Read more...
 
<< Start < Prev 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 Next > End >>

Page 1 of 67

Polls

THE INFORMATION YOU GET FROM THIS WEBSITE?